
Negeretibeb Event Organizing Plc.
በዚህ ዘርፍ የሚደረገው ጥናት በነባራዊው ዓለም በአይናችን ከምናያቸውና በስሜት ህዋሶቻችን ተጠቅመን በቀላሉ ከምንለያቸው ቁሶች በስተጀርባ በሚገኙና ባላቸው መንፈሳዊ ኃይል ምክንያት ረቀውና ተሰውረው በሰዎች አይን በማይታዩ ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያዊው አስተሳሰብ ከሆነው ከታላቋ የጥበብ መስመር እንዳገኘነው ክብረ መሰውር በፍጥረታት የአፈጣጠር ሂደት በመጀመሪያው ቀን እሁድ ዕለት የተፈጠሩት ፍጥረታት ሲሆኑ፤ በዚህ ዘርፍ የሚደረገው ጥናት ትኩረቱን በእንዚህ በማይታየው ክፍል ውስጥ የሚገኙትን ረቂቅ ምስጢራትን ተጨባጭ ወደ ሆነና ለሰው ልጆች ጥቅም ወደሚሰጥ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲቻል ግብዓት በሚሆኑና ባላቸው ታሪካዊ ዳራም ሆነ መንፈሳዊ ኃይል ተለይተው በሚታወቁ ቁሶች፣ ንዋየ ቅድሳት እንዲሁም መንፈሳዊውን ክፍል ይዘው በሚገኙ እድሜ ጠገብ ዋሻዎችና ተመሳሳይ ክፍሎች ላይ ጥልቅ የሆነ ጥናትና ምርምር ያደረጋል፡፡